ይህ ገጽ ስለትንሽ በካርታ፤ ትልቅ በዓለም የተጻፉ ውዳሴዎችን ያካትታል።
Reviews
ይህ መጽሐፍ የቦቆጂን ታሪክ ከተመሠረተችበት ከ1928 ዓም ጀምሮ እስከ 1968 ዓም ድረስ ያለውን ታሪክ ይተነንትናል። በተለይም ከተማዋ በትምሕርት ላይ ያደረገችውን እድገት እንደምሳሌ ተጠቅሞ የአካባቢውን እድገት ለመተንተን ይሞክራል።
ደራሲው ነገሠ ጉተማ
እንጂነር ነገሰ ጉተማ ቦቆጂን ከልቡ የሚወድ ሰው ነው።መውደንም በተግባር ያሳየ ባለውለታ ነው።ሀገርን መውደድ በተግባር ካልተገለጠ ብቻውን ዋጋ እንደሌለው ዋና ማሳያ ሰው ነው።አሜሪካን ሀገር አስርት አመታትን እየኖረ ቢሆንም ልቡ ቦቆጂ ነው።ፍቅሩንም እንደብዙዎች ቦቆጂን እወዳታለሁ ከማለት በዘለለ ሰፊ ጥናት አድርጎ የቦቆጂን ታሪክና የትምህርት ታሪክ አንድ ላይ አድርጎ ዳጎስ ያለ ለቀጣይ ፀሀፍት ግብአት ሊሆን የሚችል መፅሀፍን በራሱ ወጪ አሳትሞ ሙሉ ገቢውንም ለቦቆጂ አረጋውያን መርጃ ድርጅት ሰጥቷል።ኢንጂነር ነገሰ በቆጂ ከልብ ታመሰግንሀለች።ቃልን በተግባር ስላሳየህ እድሜና ጤና ይስጥልን ትልሀለች።
https://www.facebook.com/share/v/17iJqMHi1N/
አንዱአለም ጌታችሀው Dec 9, 2025
‹‹ትንሽ በካርታ፤ ትልቅ በዓለም››
ለ46 ዓመታት አሜሪካ ሀገር የኖረው ኢንጂነር ነገሠ ጉተማ ምንም እንኳን የአቅሜን ያህል የአርትኦት ሥራውን ባከናውንለትም፣ ‹‹ትንሽ በካርታ፤ ትልቅ በዓለም›› የተሰኘውን ባለ 412 ገጽ መጽሐፉን አስቀድሞም አሳምሮት ጽፎታልና በ350 ብር ዋጋ ሊሸጥ ትናንት (መስከረም 8/2015 ዓ.ም.) በበቆጂ ከተማ ተመርቋል፡፡
በአሰላ ከተማ አስተዳደር የቡርቃ ጭላሎ ባህል ኪነት ቡድን ባደመቀው መድረክ ላይ የበቆጂ ከተማ ከንቲባ በክብር እንግድነት የታደሙበት ሲሆን ከአዲስ አበባ፣ ከቢሾፍቱ፣ ከአዳማ፣ ከአሰላ እና ከበቆጂ ከተሞች እንዲሁም ከአጎራባች አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ተገኝተውበታል፡፡
ይህን መጽሐፍ የአርትኦት ሥራውን መሥራቴ ያኮራኝ መሆኑ ሳያንስ መድረኩን በሚገርም ሁኔታ በኦሮሚኛ ከመራው ከስንታየሁ ንጉሴ ጋር በተሳካ ሁኔታ መርቼዋለሁ፡፡ የመጽሐፉ አዘጋጅ የመጽሐፉን የሽያጭ ገንዘብ በቆጂ ላይ ለሚከናወን በጎ ተግባር እንዲውል ፈቅዷል፡፡
እስከ 1968 ዓ.ም. ያለውን የበቆጂ ከተማን ታሪክ ያሰፈረው መጽሐፉ ለምስረታዋ እና ዕድገቷ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሰዎች የሕይወት ታሪካቸውን ያስቀመጠ ሲሆን ስለባለታሪኮቹ እውነታውን ለማመሳከር ብዙ ሺ ሰዓታት የፈጀ የስልክ ውይይትን ከአሜራካ እየደወለ መረጃውን ሲያጠናክር ነበር፡፡
ለዚህ ድካሙ ከተለያዩ ሰዎች እና አካላት በርካታ ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን በተለይ የኦሮሞን የአለባበስ ባህል የሚያሳይ ልብስ እና ጮጮ ተበርክርቶለታል እንዲሁም የራሱን ምስል የሚያሳይ ስዕል ተሸልሟል፡፡
እንዲህ ዓይነት ታሪክን ከተሞች በዝርዝር ጽፈው ቢያሳትሙ የሚዲያ ሰዎች፣ ቱሪስቶች እና ሌሎችም ስለተጻፈለት ከተማ መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ ያስችለዋል፡፡
የምረቃውን የቀረ መረጃ የፊታችን እሑድ (መስከረም 15/2015 ዓ.ም.) በሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከሚከናወነው የአዲስ አበባው የምረቃ መርሐ-ግብር ጋር አያይዤ አቀርበዋለሁ፡፡
እስክንድር መርሐጽድቅ፣ Sept 19, 2022
የትንሽ በካርታ ትልቅ በአለም በኢንጂነር ነገሰ ጉተማ በበቅጂ ታሪክ ላይ የማያጠነጥነውን መፅሀፍ ለመመረቅ የተገኘው ህዝብ ከጠበቅነውበላይ በመሆኑ የተሰማኝን ደስታ ስገልፅ ጥራዬችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይደረስልኝ
በስነስርዓቱ ላይ ካስደነቁኝ ነገሮች
1. ይህን መፅሀፍ የፃፈው ነጌ ደራሲ ሳይሆን ብዙ መፅሐፍትን ካሳተሙ እውቅ ደረሲያን ባልተናነሰ መልኩ ረቂቁን ለኤዲትንግ በላከልኝ ወቅት ሲገርመኝ የነበረውን ትናንት ሁሌም ከእውነት ጎን ቆሞ ማዛናዊ ፅሁፎችንበማቅረብ የማደነቀው ጋዜጠኛና ደራሲው እስክንድር መርሀፀድቅ የሰጠው አስተያየት እኛን ሙያውና ልምዱን ያዳበርን ሰዎች ፃፍን ብለን እንዳንኩራራ እንገት የሚያስደፋ ድርሰት ሲል ሁሌም እውነትን በሚናገረው አንደበቱ መስክሯል
2. በቆጂ ሀገራችን በአለም መድረክ እንገቷን ቀና እንድታደርግ ባንዲራዋን ያውለበለቡ አትሌቶች እናት ከመሆኗም ባሻገር ለመልካም ነገር እንቅልፍ የለሹ ዳምጠው ነጋሽን የበቆጂ ነገር የማይሆንለት ትላንትም ፕሮግራሙን በመምራት ድምቅ እንዲል ያሳመረውን አርቲስት ካሳዬ ገበየሁን ለበቆጃ ልማትና የተቸገሩን ለመርዳት በመይነጥፈዉ ኪሱ ለስጦታ በሚዘረጉ እጆቹ የምናከብረው አት ስንታየሁ ታመነን በማንኛውም በጎ ስራ በሚደንቅ ሁኔታ የሚረበረቡት በውጪው አለም የሚኖሩ የአባባ ዝቄ ልጆችንና ስማቸውን ጠርቼ የማልጨርሰውን በውጪና በሀገር ውስጥ ያሉ የደግነት ተምሳሌት የሆኑ ልጆችችዋን አምጣ የወለደችው በቆጂ ለኔ አዲስ ሊሆን ይችላል እውቂያችን ቅርብ በመሆኑ ትላንት ለየት ያለ ሰው ጀባ ብላናለች። የጂጂቴ ሆቴል ባለቤት አቶ ገመቹ ከድግሱ ግማሽ ወጪ ነፃ፣ አዳራሽ ነፃ በስተመጨረሻም በኡስኪ ሲያራጨን ሀብት ይሉሀል ይህ ነው። በወጣ ይተካ ፈጣሪ ጨምሮ ይስጥልን ገሜ። የበቆጂና አካባቢዋ ልጆች ወደ አዳማ ስትመጡ የበቆጂን ሰው ከፈለጋችሁ ጂጂቲ ሆቴል በመጨረሻም በፕሮግራም መደራረብ መገኘት ባይችሉም የስልክ ጥሪዬን ተቀብለው ባለሁበት ድረስ ገንዘቡን አምጥተው የሰጡኝን ሀጂ ኡመር ኢብራሂም ና ልጆቹን ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ተስፋዬ ስሜ 9 Oct, 2022
****
“ይህን በልዩ ክትትል የተለፋበት መጽሐፍ የአርትኦት ሥራ በመሥራቴ ሁሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ ምክንያቱም፤ እግረ-መንገዴን ከያዘው ቁም ነገር ትልቅ ትምህርት ስለቀሰምሁ፡፡ በእውነት ነገሠ፤ ትልቅ ሰውነትህን ያስመሰከርክበት ነው፡፡”
እስክንድር መርሐጽድቅ, 28 Dec, 2025
****
“ነጌ እጅግ የድንቅ ሰብእና ባለቤት ነህ ውድ ግዜህን ሰውተህ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተህ የሙያው ሰው ሳትሆን ከሙያተኛች በሚያስንቅ ድንቅ አቀራረ አሳምረህ ስንት መስዋእትነት የከፈልክበትን ስራ ለእንደኔ አይንቱ ቲንሽ ተሳትፎ ያደረኩትን ጭምር እውቅና ስተሰጥ አንተን ዝቅ አርገህ አኛን ከፍ ስታደርግ ስለእውነት አርቆ አስተዋይነትህንና ትልቅነትህን እንድመሰክር ግድ ይለኛል። ሰዎች ፊት እራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ በእግዚአብሔር ፊት ከፍ ይላሉ ይላልና የምድሩን ቢቻ አይደለም የሰማይ ቤቱንም እየሰራህ ያለህ ወንድሜ ክብር ይገባሀል ክበርልኝ
ተስፋዬ ስሜ.
****
“በህይወት ዘመኔ ከአነበብኳቸው ምርጥ መጽሐፎች አንደኛው ይህ በኢንጅነር ነጌ የተጻፈው ነው። በርካታ ብዥታዎቼ የጠሩበት፣ትምህርት የቀሰምኩበት፣ቁምነገረኛ ሰዎችን ያገኘሁበት፣ የበቆጂን ተወላጆችና ወዳጆች ትብብር ጎልብቶ ያየሁበት፣የነጋሽ ገ/እግዚአብሔርን ልጅ ሁለገብ አስተባባሪነት ያየሁበት ፣የተስፋዬ ስሜን ከጤና ውጭ የጽሑፍ ችሎታ ያየሁበት፣ የአንኪቲን የተለመደ ኮስታራ አስተያየት የደጋገምኩበት፣ በአካል ባላውቀውም መስፍን ኃይሌ የሚባል ልጅ አስተዋጽኦ ምሳሌ የሆነበት ...ኧረ ስንቱን ዘርዝሬ ልቻለው። አንጅነር በርካቶችን አሰባስበህ ትውልዶችን አስተዋውቀህ ስለሰጠኸን ቁምነገር እጅህ ይባረክ! Harka kee qoreen hin waraanin! /Qalamni kee yaa mirgu!።ይላል የሀገራችን ሰው ሲተርት እንደ ኢንጅነር አይነቱን"፤ እኛም ብለናል። ቅጽ ሁለትን ለማንበብ ያብቃን!!!
ግርማ ባልቻ፣ 30 Dec 2025
****
“ይህ መፅሐፍ እንደ በቆጂ ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ትልቅ ግብአት እንደሚሆን አምናለሁ::”
መስፍን ኃይሌ፥ 27 Dec, 2025
****