Negesse Gutema is a native of Bekoji, an author, a community leader, and a father.
Book Debut
ትንሽ በካርታ፤ ትልቅ በዓለም
Tinish Bekarta Tiliq Bealem:
History of Bekoji and Its Education
"ትንሽ በካርታ፤ ትልቅ በዓለም" (Tinish Bekarta: Tiliq Bealem") is a history of a small town in Arsi Zone known as Bekoji and its educational progress written by one of the co-founders of YESSERA (Young Ethiopian Self Sufficiency Enhancing Re-education Association), a non-profit started in 2001.
Overall, the book provides a good picture of the demographic changes of the people of Becojji and its vicinity. The stories the author collected from former students provide the individuals’ success, but it is also a great tribute to all the teachers. The testimony of the former students about their teachers provided fascinating biographies of the former teachers. It is an excellent tribute to the collective works of all the teachers of Becojji.
- Dr. Solomon Gashaw
እኔ እስከማውቀው ድረስ ስለበቆጂ ሁሉንም ሁኔታዎች ባጠቃለለ መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀረበ ይህ የኢንጂነር ነገሠ ጉተማ መጽሐፍ ብቻ ነው። የተጻፈውም ሰፋ ባለና ብዙ የተለያዩ ዲሲፕሊኖችን (Broad interdisciplinary perspective) ባቀፈ እይታ ነው። ስለዚህም የዚህ መጽሐፍ ርእስ፣ “የበቆጂና የሕዝቡ ታሪክ ከሕበረሰባዊ ታሪክ አመለካከት (A Socio-Historical Perspective of Bekoji and its People)” ቢሆን እወድ ነበር።
የኢንጂነር ነገሠ መጽሐፍ ለአጠቃላዩ ከአካዴሚክ ዓለም ውጭ ላሉ አንባቢያን እጅግ በጣም ጥሩ ምንጭ (ግባዓት) ሲሆን፤ ለተለያዩ የትምሕርት ተቋማት ደግሞ የላቀ የማስተማሪያ ግብአቶች ያሉት ሰነድ ነው። እንደ ታሪክ፣ ሶሺዮሎጂ እና ማሕበራዊ አንትሮፖሎጂ ያሉ የተለያዩ የዲሲፕሊን አካሄዶችን ስላቀናጀ መጽሐፉ የኢንተርዲሲፕሊናዊ እይታ መገለጫ ነው። ለምሳሌ፥ የኢጣሊያ የቅኝ አስተዳደር ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር የነበራቸውን ማሕበራዊ መስተጋብር አስመልክቶ የጻፈው ሰነድ ለማሕበራዊና ታሪካዊ ዘዴ አጻጻፍ ጥሩ ምሳሌ ነው። በተጨማሪም ቃለ መጠይቆችን እና የቃል ወጎች አቀናጅቶ አዋህዷል። በመጨረሻም የአስደናቂ ፎቶግራፎች ስብስብ ማካተት አሁን የማይገኙ ቦታዎች ምስሎችን ለአንባቢዎች ያቀርባል።
ሌላው የዚህ ሥራ ጉልህ አስተዋፅኦ ኢንጂነር ነገሠ በርካታ የአካባቢ አስተዳደር ሰነዶችን ሰብስቦ በመጠቀሙና ከማሕበረሰቡ የቃል ወጎች እና እውቀት ካላቸው ሰዎች ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ ጋር ለማመሳከር መቻሉ ነው። በተጨማሪም የግለሰብ ታሪክ (ባዮግራፊያዊ) መረጃ እና የተቋማት፣ የትምሕርት ቤቶች እና የማዘጋጃ ቤት አስተዳደር እድገት ስለከተማ የእድገት ሂደት (The evolution of urbanization) ለማስተማር ጥሩ ናቸው። በእኔ እምነት መጽሐፉ የበቆጂ ከተማን እና የትምሕርት ቤቱን ተቋማዊ እድገት ከሁለት ክፍል የሳር ቤት እስከ ውስብስብ ዘመናዊ ከፍተኛ ተቋማት መድረስን ያሳያል።
ደራሲው ከቀድሞ ተማሪዎች የሰበሰባቸው ታሪኮች የግለሰቦችን ስኬት ሲያሳይ ለሁሉም መምሕራን ደግሞ ታላቅ ክብርን አጎናጽፏል። የቀድሞዎቹ ተማሪዎች ስለ መምሕራናቸው የሰጡት ምስክርነት የመምሕራኑን አስደናቂ የሕይወት ታሪክ እንድናውቅ ረድቶናል። ይህም ሁሉም የበቆጂ መምሕራን በአንድነት ሆነው ትምሕርትን ለማስፋፋት ላደረጉት ሥራዎች ታላቅ ውዳሴ ሆኖ ያሳያል። መጽሐፉ ፈር ቀዳጅ መምሕራን በእኔም ላይ ያሳደሩትን አወንታዊ ተፅዕኖ ወደኋላ ተመልሼ እንዳሰላስል ጥሩ አጋጣሚ ሰጠኝ። ረዥም ቁመና በነበረውና በአስደማሚው (ካሪዝማቲክ) መምሕር ሥዩም መንገሻ አስተማሪነት ያገኘሁትን የመጀመሪያ ቀን የክፍል ልምዴን በደንብ አስታውሳለሁ፤ እስከዛምሬ የሚያስደምም ተሞክሮ ሆኖ ከኔ ጋር ቆይቷል። ከክፍል ውስጥ ትምሕርትም አልፎ አጠቃላይ አወንታዊ ተፅዕኗቸው በውስጤ ተተክሏል። የመምሕር መንግሥቱ ሳህለ ማርያም፣ መምህር መሥፍን አበበ፣ መምህር በቀለ ጉተማ እና የሁለቱ ዳይሬክተሮች መምሕራን ሙሉጌታ እና ሞገስ ማበረታቻ እና ምክር ዘላቂ የሆነ አወንታዊ ተፅዕኖ ጥለውብኛል።
እንጂነር ነገሠ የተለያዩ ባለሙያዎችን፣ መምሕራንን፣ የአትሌቶችን፣ የሕክምና ዶክተሮችን፣ ወዘተ ታሪክ ሰብስቦ ለዚህ ቁም ነገር አድርሷል። በአጠቃላይ መጽሐፉ የበቆጂ እና አካባቢው ሰዎች የስነ-ሕዝብ አወቃቀር ለውጦችን ጥሩ ምስል ያቀርባል። ሌሎችም የኢንጂነር ነገሠ ጉተማን ፈር ቀዳጅ ሥራ እንደሚቀጥሉበት ተስፋ አደርጋለሁ።”
ዶር ሰለሞን ጋሻው፣ ፕሮፌሰር ኤመሪተስ
ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ (ሞሪስ፣ ሚኔሶታ)
“This is not only the history of Bekoji but also of Ethiopia.”
— Negesse Gutema
Community Stewardship: YESSERA
YESSERA (Young Ethiopian Self Sufficiency Enhancing Re-education Association) was founded by a group of friends, including Negesse Gutema, in 2001 with the mission to help provide youth in Ethiopia with the immediate hands-on training to immerse in the workforce in order to improve their economic status.
This organization is run by dedicated volunteers that are passionate about working towards a brighter future.
Supporting Seniors in Bekoji
Bekoji has a considerable number of Senior Citizens who are over 60 years old. These retired elders were educators, farmers, soldiers, police officers, shop keepers, handymen, government employees, etc. who served their country and community without reservation.
Now in their retirement age, they need a center to congregate and continue being productive citizens and contribute to the growth of their community. Bekoji Elders were organized by the districts administration as a nonprofit organization in 2003 EC (2011 GC). They have been looking for a home ever since then.
We are raising funds to establish this center where they can spend their time together; support themselves and continue to give back to the community by mentoring and tutoring the youth, by practicing traditional conflict resolution methods, and through many other services.
In the News
Negesse Gutema speaks about his new book and the history of Bekoji to continue to educate the community about the significance of this small town in the broader historical and contemporary story of Ethiopia.
Contact
Feel free to contact us with any questions.
Email
negesse.gutema.author@gmail.com